የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርስኖ አቡሬ

‎የፍትሕ ሥርዓቱን ነፃ ገለልተኛና ጥራት ያለው ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፦​ አቶ ኤርስኖ አቡሬ‎

‎ጥቅምት 2019 

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመራሮች ጋር የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ለይ የውይይት መድረክ ተካሄዷል።

‎​በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርስኖ አቡሬ እንደተናገሩት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥና የዜጎች መብት እንዲጠበቅ ፍርድ ቤቶች ነፃ፣ ገለልተኛና በሕግ ብቻ የሚመሩ መሆን አለባቸው ብለዋል።

‎አገልግሎታችንን ይበልጥ የተሻለና ጥራት ያለው ለማድረግ እየሰራን የነበረውን ጥረት ይበልጥ ቀጣይነት እንዲኖረው ሁላችንም አጠናክረን መስራት ይገባናል ሲሉ አቶ ኤርስኖ አቡሬ ተናግረዋል።

‎አቶ ኤርስኖ አቡሬ አክለውም የዳኝነት አገልግሎቱን ይበልጥ ግልጽ ቀልጣፋ ተደራሽ እና ተገማች በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና እርካታ ማሳደግ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።

‎በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዳኝነት አገልግሎትን በማስፋፋት የፍትሕ አሰጣጡን ቀልጣፋና ከእንግልት የጸዳ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

‎ብልሹ አሠራርና ሙስናን በመከላከል የርቀት ችሎቶችን አጠቃቀም አዲሱን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ እንዲሁም የፕሮቶኮል አያያዝ ረቂቅ ሰነዶችን በቁርጠኝነትና በቅንጅት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

‎​ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት የባህላዊ ዳኝነት ሥርዓት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ሥርዓት ከሕጋዊ ማዕቀፍ ጋር በማቀናጀት ከዘመናዊው የፍትሕ አሰጣጥ ጋር በጋራ መምራት እንደሚያስፈልግ ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ እንዳርጋቸው ይድነቃቸው እንደገለፁት ሕገ-መንግሥቱን ባከበረና ግልጽነት ባለው አሠራር ዜጎች የሚገባቸውን ፍትሕ እንዲያገኙና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል።

‎ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዜጎችን የፍርድ ቤት ቅሬታዎች በወቅቱ በመመርመርና ፈጣን ምላሽ በመስጠት የሕዝብን እምነትና እርካታ ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

‎በመድረኩ የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች የተገኙ ሲሆን፤ ከተሳታፊዎቹ ሰፋ ያሉ ሐሳቦች ቀርበው ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንድአርጋቸዉ ይድነቃቸዉ

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

‎ጥቅምት 2/2019

‎በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንድአርጋቸዉ ይድነቃቸዉ የዘንድሮ ፍርድ ቤቶች የስራ ማስጀመሪያ የሆነዉ ጥቅምት አንድ ከባለፈዉ አመት የዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ጥቅማ ጥቅም በመመሪያ ቁጥር 74/2018 በተከበረበት ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 01/2016 አንቀጽ 59/2 መሠረት የክልሉ ፍርድ ቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ አንድ እሰከ መስከረም ሰላሳ ድረስ ዝግ ሆኖ እንዲቆይ መወሰኑን ተናግረዋል።

‎በዚህ መሠረት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጀምሮ እስከ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ድረስ ከነሀሴ 01 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 30 /2019 ዓ/ ም ድረስ በከፊል ዝግ ሆነዉ ለአስቸኳይ ጉዳይ ብቻ ተረኛ ችሎት ተመድቦላቸዉ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር መደበኛ ሙግቶች አለመከናወናቸዉን ተናግረዋል።

‎በሀገራችን ኢትዮጲያ ፍርድ ቤቶች ከሶስቱ የመንግስት አካላት አንዱ የሆነዉ ፍርድ ቤት ነፃና ገለልተኛ ተቋም በመሆን በህገመንግስቱ ሲቋቋም ለህዝብ የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎት ፈጣን፣ ተደራሽና ተገማች እንዲሁም ከአድሎ የጸዳ የፍትህ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም አክለዋል።

‎በ2018 በጀት አመት የክልሉ ፍርድ ቤቶቻችን በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በወንጀልና በፍትሐብሔር የቀረቡ መዝገቦችን ዉሳኔ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ዉጤት የተመዘገበ አመት እንደነበር ጠቅሰዋል።

‎የተመዘገበዉን የተሻለ አፈጻጸም በ2019 በጀት አመት ይበልጥ ለማሻሻል ቃላችንን አድሰን በአዲስ ሞራል ወደስራ የምንገባበት ጊዜ መሆኑንም ገልጸዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መስማትና መወሰን ስራሂደት አስተባባሪ አቶ ሸረፋ አሊ በበኩላቸው በባለፈዉ አመት የመዝገብ ክምችት መኖሩን ጠቅሰዉ በተቻለ መጠን የመዝገብ ክምችቱን በዉስን ዳኞች የማጣጣም ስራ እየተሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

‎የ2019 ዓ/ም የስራ ማስጀመሪያ እንደ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በርካታ አዳዲስ ዳኞች በመቀጠራቸዉ የቀጠይ 2019 ዓ / ም የዳኝነት ስራ አፈፃፀሙን ከባለፈዉ ዓመት የፍትህ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ፍታሐዊ ለማድረግ አቅደዉ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

‎የሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሰኢድ አደም የዳኝነት ስራ ዳኞች የሚቀርብላቸዉን መዝገብ በመቀበል ለህዝብ የሚሰጡትን አገልግሎት ምን እንደሚመስል የመከታተል ስራ እንደሚሰሩ ጠቅሰዉ የዳኝነቱን ስራ በቅንነት፣ በታማኝነት እና በገለልተኝነት በተቀላጠፈ መልኩ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

‎አቶ ሰኢድ አክለወም የ2019 ዓ/ም የሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ የዳኝነት ስራ ከጥቅምት ሁለት ጀምሮ በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

 
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት መልዕክት

    አቶ ኤርስኖ አቡሬ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ  መሠረት በክልሉ የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን የተሰጠዉ ህግ ተርጓሚ የመንግስት አካል ነዉ፡፡

ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጡ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አግባብ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ህግና ማስረጃን መሰረት በማድረግ እልባት መስጠት የሚጠበቅባቸዉ በመሆኑ የዜጎችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ረገድ የፍርድ ቤቶች ሚና የጎላ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ለዉጤታማነቱ የሚኖረዉ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅዶ እየሠራ ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋለዉን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ፍኖተ- ካርታ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያሻሻለ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተገማች የሆነ ዳኝነት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ስለሆነ ህዝባችን ከጎን በመሆን ድጋፍ እንዲሰጠን እጠይቃለሁ ፡፡

የዳኝነት ተደራሽነትና  ቅልጥፍናን ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ የማዘመን ሥራ እየሠራን ስለሆነ የክልላችን ዳኞች ፣የህግ ባለሙያዎችና የአሰተዳደር ሠራተኞች ከተገልጋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና ጠንክረን በመሥራት የህዝባችን የዳኝነት ጥያቄን በታማኝነት፣በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት በመወጣት የህዝባችንን አመኔታ ለማትረፍ እንድንረባረብ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ 

ከ 1985 ዓ.ም ጀምሮ ፍርድ ቤቱን የመሩት ፕሬዝዳንቶች

"Image"Image 2Image 3Image 4Image 4Image 6

የማ/ኢ/ክ/ጠ/ ፍርድ ቤት ስራ ሂደቶችና ዳሬክቶሬቶች

መስማት እና መወሰን ሥራ ሂደት
አቶ ኃብታሙ አብነው  
መስማትና መወሰን ስራ ሂደት ዳይሬክተር
የተከላካይ ጠበቃ
አቶ ቢኒያም ከበደ 
የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ
የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ በለጠ ስልኮራ 
የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ
የሸርዓ ፍርድ ቤት ዋና ቃዲ
ሸክ አብራ ሽፋ 
የማ/ኢ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቃዲ
የዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
አቶ እሸቱ ደቦጭ የዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት
ሰለሞን መሽሻ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት
ስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳሬክቶሬት
አቶ ታምራት አቤቦ 
ስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳሬክቶሬት
የልማት ዕቅድ ክ/ግ/ግ ዳይሬክቶሬት
አቶ መኮንን ተሻለ  
የልማት ዕቅድ ክ/ግ/ግ ዳይሬክቶሬት
የሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት
አቶ ኤርሚያስ ኦልከሞ
የሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት
ፋይናንስ ዘርፍ ዳሬክቶሬት
አቶ ሱልጣን ሙሰማ 
ፋይናንስ ዘርፍ ዳሬክቶሬት
ኦዲት ዳሬክቶሬት
አቶ አክሊሉ ታደስ
ኦዲት ዳሬክቶሬት

 

ሪከርድ እና ማህደር የስራ ሂደት
ወ/ሮ አስቻለች ሀይሌ 
ሪከርድ እና ማህደር የስራ ሂደት

Latest News

Media

ከ 1985 ጀምሮ ፍርድ ቤቱን የመሩት ፕሬዝዳንቶች

አቶ ኤርስኖ አቡሬ 
  የማ/ኢ/ክ ጠቅላይ ፍርድቤት የአገልግሎት ዘመን ከጥቅምት 14/2014 ዓ/ም ጀምሮ - አስካሁን
አቶ ሙሉጌታ አጎ ወ/ሚካኤል 
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን 8/06/06-ጥቅምት 24/ 2014 ዓ/ም
አቶ ታረቀኝ አበራ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከህዳር 18/03/99-ታህሣስ 18/04/06 ዓ/ም
አቶ ፍሬህይወት ሳሙኤል 
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከ12/02/1996- 18/06/99 ዓ/ም
አቶ በየነ ቢልቱ ኮልቤ 
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከየካቲት21/06/89-ጥቅምት 12//02/96 ዓ/ም
አቶ ደምሴ ሎዶቦ አማጦ 
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከ1985-የካቲት8/06/1989 ዓ/ም

አስተያየት ካለዎት ከስር ባለው ፎርም ይጻፉልን/ይሙሉ፡፡

One file only.
2 MB limit.
Allowed types: txt.