Skip to main content

 

 

አቶ እሸቱ ደቦጭ
 የዋና ጉባዔ ጽህፈት ቤት  ኃላፊ

 

 

 

 

 

 

የዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ስልጣንና ተግባር 
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ተጠሪነት ለዋና ጉባዔው ሰብሳቢ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡- 
1)  በአዋጅ ቁጥር 2/2016 በአንቀጽ 22 ድንጋጌ መሠረት ለጽህፈት ቤቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ስራ ላይ ያውላል፤ 
2)  የንኡስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የጽህፈት ቤት ኃላፊው የሚከተሉት ስልጣንና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡- 
ሀ) ድምጽ የመስጠት መብት ሳይኖረው ጉባዔውን በፀሐፊነት ያገለግላል፣ 
ለ) የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ይይዛል፣ ቃለ-ጉባዔዎችና ሌሎች ተዛማጅ ሰነዶች በጉባዔው አባላት መፈረማቸውንና በጥንቃቄ መያዛቸውን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፣ 
ሐ) ከጉባዔው ሰብሳቢ ጋር በመነጋገር የጉባዔውን አጀንዳዎች ያደራጃል፣ ከጉባዔው ስብሰባ ቀን አስቀድሞ አጀንዳዎቹን ለአባላት ያሰራጫል፣ መድረሳቸውንም ይከታተላል፣ 
መ) የጽህፈት ቤቱንና በሥሩ ያሉ የሥራ ክፍሎችን የዕለት-ተዕለት ሥራዎች በኃላፊነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል፣ 
ሠ) የጉባኤው የተለያዩ ኮሚቴዎች ቢሮ በማደራጀት የኮሚቴዎቹን ባለሙያዎችና ረዳት ሠራተኞችን ያሰማራል፣ 
ረ) የጉባዔውን ረቂቅ ዓመታዊ የሥራ እቅድ እና የማስፈጸሚያ በጀት አዘጋጅቶ ለጉባዔው ሰብሳቢ ያቀርባል፣ 
ሰ) የጉባዔውን የስራ እቅድና አፈጻጸም አስመልክቶ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፣ 
ሸ) የጽህፈት ቤቱን ሠራተኞች ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤ 
ቀ) በጉባዔውና በሰብሳቢው የሚሰጡትን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡

                                የዳኝነት ነጻነት

  1. በየትኛውም እርከን የሚገኝ የክልል ፍርድ ቤት ወይም ዳኛ ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ባለሥልጣን ወይም ሌላ አካል ተፅዕኖና ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ ሥራውን በሕግ መሰረት ያከናውናል፤
  2. ዳኞች ስራቸውን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ተጽዕኖ ነጻ ሆነው በማከናወን በሕግና ፍሬ-ነገር ላይ የተመሰረተ ፍርድ፣ ብይን፣ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ይሰጣሉ፤
  3. ማንኛውም የመንግሥት አካል፣ የመንግሥት ባለሥልጣንም ሆነ ሌላ ማንኛውም ሰው የክልሉን ፍርድ ቤቶች ተቋማዊና የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት የማክበር ግዴታ አለበት፤
  4. ማንኛውም የመንግሥት አካል፣ የመንግሥት ባለሥልጣንም ሆነ ሌላ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ፣ ውሳኔ፣ ብይን ወይም ትዕዛዝ የማክበርና የመፈጸም ግዴታ አለበት፤
  5. የክልሉ ፍርድ ቤቶች በበጀት፣ በሰው ኃይል አስተዳደር እና በውስጥ አሰራራቸው  እራሳቸውን ችለው ይሠራሉ፡፡

                               የዳኝነት ተጠያቂነት

  6. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የክልል ፍርድ ቤት ከተሰጠው ኃላፊነት አንጻር በሕግ መሠረት ተጠያቂነት አለበት፤
  7. ዳኞች የያዙት ክርክር ሂደት ተከራካሪ ወገኖችን ያለአድሎዎ በእኩልነት የሚያስተናግዱ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴት ይኖርባቸዋል፤ በተለይም በወንጀል የተከሰሱ ወይም በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎችን አያያዝ ሁኔታ የመከታተል፤ ሰብአዊ መብቶቻቸውን የማክበር እና የማስከበር የእነዚህ መብቶችን ጥሰት የሚመለከት አቤቱታ በቀረበ ጊዜም ጉዳዩ አግባብ ባለው አካል ተጠርቶ ተገቢው እንዲፈፀም ትዕዛዝ የመስጠት ሃላፊነት አለባቸው፡፡
  8. በሌሎች ሕጎች የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ዳኛ የዲሲፕሊንና የሥነምግባር ጥፋት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ በዳኝነት አስተዳደር ዋና ጉባዔ የዲሲፕሊን ደንብ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡