
አቶ ኃብታሙ አብነው
የጠቅላይ ፍርድ ቤት መስማትና መወሰን ስራ ሂደት አስተባባሪ
የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ሥልጣንና ተግባር
አቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ተጠሪነቱ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚከተለው ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-
- የሥራ ሂደቱን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤
- ተጠሪ ለሆነለት አካል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤
- ለስራ ሂደቱ የሚመደብለትን ዓመታዊ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ያደርጋል፤
- በጉዳዮች መለኪያ ወይም ስታንዳርድ መሠረት በሥሩ ለሚገኝ የሥራ ክፍል የሥራ ስምሪት ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የሥራ ሂደቱን ሥራዎች በበላይነት ያስተባብራል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
- ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞችን በመለየት ችግር ፈቺ በሆኑ ሀሳቦች ላይ የስራ ሂደቱን አባላት ያወያያል፣ መፍትሔ ይሰጣል፤
- የመዝገቦችን ብዛት እና የጉዳዮችን ፍሰት እያጠና የተሻለ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ለምክትል ፕሬዝዳንቱ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በሥሩ በሚገኙ ችሎቶች የሚያስችሉ ዳኞች ተሟልተው ማስቻላቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ይከታተላል ፣ይቆጣጠራል፣ ጉድለት በታየ ጊዜም ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር በመመካከር ተገቢውን ማስተካከያ ያደርጋል፤
- ከመዛግብት ጋር በተያያዘና የስራ ሂደቱን በሚመለከት በባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ መፍትሔ ይሰጣል፤
- የስራ ሂደቱን አባላት የሥነ-ምግባር ሁኔታ ይከታተላል፣ የሚታዩ ጉድለቶችንም በመለየት የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ እንደአጥፊው ማንነት ለንኡስ ጉባዔ ጽህፈት ቤት ወይም ለአስተዳደር ሠራተኞች የሰው ሐብት አስተዳደር ያቀርባል፤
- በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤
- በዞን፤ ልዩ ወረዳ፤ በወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ተጠሪነት ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ እንደአግባብነቱ በዚህ አንቀጽ የተዘረዘሩ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
046-55-62-112




