
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት መልዕክት
አቶ ኤርስኖ አቡሬ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ መሠረት በክልሉ የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን የተሰጠዉ ህግ ተርጓሚ የመንግስት አካል ነዉ፡፡
ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጡ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አግባብ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ህግና ማስረጃን መሰረት በማድረግ እልባት መስጠት የሚጠበቅባቸዉ በመሆኑ የዜጎችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ረገድ የፍርድ ቤቶች ሚና የጎላ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ለዉጤታማነቱ የሚኖረዉ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅዶ እየሠራ ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋለዉን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ፍኖተ- ካርታ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያሻሻለ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተገማች የሆነ ዳኝነት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ስለሆነ ህዝባችን ከጎን በመሆን ድጋፍ እንዲሰጠን እጠይቃለሁ ፡፡
የዳኝነት ተደራሽነትና ቅልጥፍናን ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ የማዘመን ሥራ እየሠራን ስለሆነ የክልላችን ዳኞች ፣የህግ ባለሙያዎችና የአሰተዳደር ሠራተኞች ከተገልጋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና ጠንክረን በመሥራት የህዝባችን የዳኝነት ጥያቄን በታማኝነት፣በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት በመወጣት የህዝባችንን አመኔታ ለማትረፍ እንድንረባረብ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
046-55-62-112




