የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር በኢትዮ-ኮደርስ ፕሮግራም ስልጠና ዙሪያ ለዳኞች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል። በመርሀግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ኤርስኖ አቡሬ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ሀገር "5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ዜጎች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት ኖሯቸው ስራ እንዲፈጥሩና ሀብት በማካበት ሀገራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚን እንዲያስቀጥሉ የሚረዳ ፕሮግራም መሆኑን አስረድተዋል። ሰራተኛው በዲጂታሉ አለም ተወዳዳሪ መሆን ይችሉ ዘንድ በፕሮግራሙ ላይ ስልጠና የጀመሩ ዳኞች አጠናክረው እንዲቀጥሉና ሌሎችም የፐብሊክ ሰራተኞች ይህንን ስልጠና በቀጣይ በትኩረት መሰልጠን ይገባቸዋል በማለት አሳስበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ የሶፍት ዌር አበልፃጊና አስተባባሪ አቶ መንሱር ሀምዛ በስልጠና መረሀግብሩ ላይ አጠቃላይ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሂደት ምንነት ላይ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስተር አመቻችነት ለሀገራችን ዜጎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የለቀ እውቀት እንዲያካብቱ ታቅዶ የመጣ ሶፍት ዌር የስልጠና መረሀ ግብር መሆኑን አብራርተዋል።
046-55-62-112




